የጭስ ደወሎች ሰዎችን ከጭስ አደጋ በማንቃት ህይወትን ያተርፋሉ። ጭስ መርዛማ ነው። በእሳት ውስጥ ብዙ ሰዎችን የሚገድል ነገር ነው። የጭሱን ደወል በቁም ነገር መወሰዱ እና ሲጮህ በፍጥነት እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ነው። የጭስ ደወሎችን መቼም ቢሆን አይሸፍኑ፣ ቀለም አይቀቡ ወይም አያስወግዱ። በየዓመቱ ወይም የጭስ ደወሉ ጭል ጭል የሚል ድምጽ ሲያወጣ ባትሪዎችን መቀየር ያስታውሱ።
የጭስ ደወሉ ከጮኸ፡-
1. እሳት ፈጥኖ ይሰራጫል። ፈጥነው ይውጡ እና ውጪ ይቆዩ።
2. ከተቻለ፣ እሳቱን ለመቆጣጠር በሮችን ይዝጉ።
3. ጭስ ካጋጠምዎት፣ በደረትዎ ተንፏቀው ወደ መውጫው ይሂዱ።
4. ውጪ ወዳለው መገናኛ ቦታ ይሂዱ እና በተቻለ ፍጥነት ወደ 9-1-1 ይደውሉ። እንግሊዝኛ የማይናገሩ ከሆነ ለኦፐሬተሩ/ሯ ቋንቋዎን ይናገሩ።
5. አንዴ ከወጡ፣ እንደወጡ ይቆዩ። ወደሚቃጠል ህንጻ መቼም ቢሆን አይመለሱ።
May 19
የጭስ ደወሎች – የጭስ ደወል ሲጮህ ምን መደረግ አለበት – ማምለጥ እና 9-1-1 (Smoke Alarm Safety in Amharic)
0 comments