ምግብ የማብሰል ደህንነት
አብዛኞቹ የቤት ውስጥ የእሳት አደጋዎች የሚነሱት በማዕድ ቤት ውስጥ አንድ ሰው ማብሰል ጀምሮ በማንደጃው ላይ ያለውን ምግብ ሲረሳ ነው። በሰው፣ በስልክ ጥሪ ወይም በኤሌክትሮኒክ እቃ ትኩረት በቀላሉ ሊወሰድ ይችላል። እሳት በሰኮንዶች ውስጥ ሊነሳ ይችላል።
እንዴት እራስን መጠበቅ እንደሚቻል፡-
1. በዘይት ወይም በቅባት ሲያበስሉ በማዕድ ቤት ይቆዩ
2. ምድጃው መብራቱን እንዲያስታውሱ ሁልጊዜ ሰዓት መያዣ ይጠቀሙ
3. የምድጃውን አካባቢ ንጹህ አድርገው ይያዙ
4. ድንገት እሳት ቢነሳ ብለው በምድጃው አካባቢ ክዳን ያስቀምጡ
• በቅባት ወይም በዘይት እሳት ላይ መቼም ቢሆን ውሃ እንዳይጨምሩ
• በትንሽ መጥበሻ ላይ የተነሳ እሳትን ለማጥፋት ምርጡ መንገድ በድስቱ ወይም በመጥበሻው ላይ ክዳን መክደን ነው።
• ማንደጃውን ያጥፉ
• የሚነድ መጥበሻን ለማንቀሳቀስ አይሞክሩ።
• እሳቱ ከጠፋ እና ከቀዘቀዘ በኋላ ብቻ ክዳኑን ያንሱ።


Tags

Seattle Fire Department, Seattle Fire, Seattle Fire Rescue, Seattle Fire Medics


You may also like

Shaped By Fire (2022 Documentary)

Subscribe to our newsletter now!